የዋስትና (“ንያሮት ዔሬኽ”) ባለሥልጣን የተመሠረተው እ.ኤ.አ በ1968 ዓ.ም. ሲሆን በ“ንያሮት ዔሬኽ” ባለሥልጣን ሕግ ላይ ተመሥርቶ ነው። ሕጉ በወሰነው መሠረት የሥራ ተግባሩም በ“ንያሮት ዔሬኽ” መዋዕለ ንዋይ ያፈሰሱ ባለሀብቶችን (“ኢንቨስተሮችን”) ጉዳይ ማስፈጸም ነው። ባለሥልጣኑ በሥራ ድርሻው መዋቅር ውስጥ፣ ከሌሎች ሥራዎች በተጨማሪ፣ የሚከተሉትን ጉዳዮች ይንከባከባል፡-
ትንበያዎች በመገናኛ ብዙኃን ሆነ በኅትመት ለሕዝቡ እንዲገለጹ ፈቃድ መስጠት። ኩባንያዎች በዚህ ትንበያ ላይ ተመሥርተው ነው ለሕዝቡ “ንያሮት ዔሬኽ” የሚያቀርቡት። “ታሽኪፍ” የተሰኘው ሰነድ “ንያሮት ዔሬኽ”ን ለሕዝብ የሚያቀርብ ኩባንያ የሚያዘጋጀው ሲሆን “ንያሮት ዔሬኽ”ን ለመግዛት ለሚያስብ ሰው በቂ የሆነ ግልጽ መረጃ የሚሰጥ ነው። ትንበያው በተጨማሪ የሚያካትተው ለሕዝቡ የቀረበውን የ“ንያሮት ዔሬኽ” ዝርዝር፣ የድርጅቱን የንግድ ሥራ ዝርዝር እና የገንዘብ ዘገባ ነው።
የ“ክራኖት ነኤማኑት” ተግባራት ሥነ ሥርዓት እንዲይዙ ያደርጋል እንደዚሁም “ክራኖቱን” ይቆጣጠራል። በዚህ የሥራ ድርሻው ባለሥልጣኑ እያንዳንዱ “የኬሬን ነኤማኑት” ክፍል ትንበያውን እንዲያቀርብ እና በብዙኃን መገናኛ ማሳወቅ እንዲችል ፍቃድ ይሰጣል። የ“ኬሬኑ” የትንበያው ሰነድ የሚያጠቃልለው፡- እያንዳንዱ ክፍል የሚያቀርበውን ሐሳብ፣ የ“ኬሬኑ”ን ንብረት በታማኝነት ስለሚያስተዳድረው ድርጅት ዝርዝር፣ የ“ኬሬኑ” የኢንቨስትመንት (ገንዘብን ሥራ ላይ የማዋል) መመሪያ፣ የ“ኬሬኑ” የንብረት ይዘት የሚመለከቱ መረጃዎች፣ የቅርንጫፉ ትርፍ ከ“ንያሮት ዔሬኽ” መለኪያዎች አንጻር፣ ስለ ቅርንጫፉ የገንዘብ ዘገባ እና እንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎችን ነው። ክፍት የሆነ “ኬሬን” ትንበያ አገልግሎት ጊዜ ለሕዝብ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ እስከ 12 ወራት ብቻ ነው። ስለዚህ “የኬሬን ነኤማኑት” ክፍሎች የሚያቀርቡትን ሐሳብ ቀጣይነት ለማረጋገጥ “የኬሬን ነኤማኑት” አስተዳደር ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ በብዙኃን መገናኛ ወይም በኅትመት ለሕዝቡ ማሳወቅ አለበት።
እያንዳንዱ ለሕዝቡ “ንያሮት ኤሬኽ” ያቀረበ “ኮርፖሬሽን (“ታአጊድ”) ተከታታይ ሪፖርት ማቅረብ ስላለበት በዚህ ሪፖርት ላይ ድርጅቱ ክትትል ማድረግ አለበት። ይህም የሚሆነው “ንያሮት ኤሬኽ” በሕዝቡ እጅ እስከሆኑ ድረስ ነው። “ንያሮት ኤሬኽ” ገበያ ላይ ከዋሉ በኋላ ባለሀብቶችን ስላሉት ለውጦች ማሳወቅ ስለሚያስፈልግ “ኮርፖሬሽኑ” በዓመት አንድ ጊዜ የገንዘብ ሰነድን ያካተተ ወቅታዊ ዘገባ፣ ስለ ኮርፖሬሽኑ” “ዲሬክቶሪዮን” የሚያቀርበውን ዘገባ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ያቀርባል። እንደዚሁም “ኮርፖሬሽኑ” በየ3 ወሩ የ3 ወር ሪፖርት ያቀርባል። ይህም ሪፖርት የገንዘብ ዘገባን፣ የዲሬክቶሪዮን ዘገባን እና እንዲሁም በ“ኮርፖሬሽኑ” ላይ ወይም በ“ንያሮት ኤሬኽ” ላይ ከፍተኛ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ክስተቶች ካሉ ወዲያውኑ ማስታወቅ አለበት። በተጨማሪም ባለሥልጣኑ “ክራኖት ኔኤማኑት” በሚያቀርቡት ተከታታይ ሪፖርት ላይ ክትትል ያደርጋል።
ለግዢ ድርድር በሚቀርቡ ዝርዝሮች ላይ ክትትል ማድረግ። የግዥ ድርድር (“ሃጻአት ረኸሽ”) የሚባለው ከሕዝቡ ላይ የ“ኮርፖሬሽኑን” “ንያሮት ኤሬኽ” መግዛት ለሚፈልግ ሰው እንደመመሪያ የሚያገለግለው መሣሪያ ነው። ይህም የባለቤትነት ይዞታን (“ሃሕዛኮት”) ለሚፈጥሩ ወይም የባለቤትነት ይዞታቸውን ከፍ ለሚያደርጉ (እስከ መቶ ፐርሰንት ድረስ) ወይም ኮርፖሬሽኑን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ለሚፈልጉ ሰዎች ጭምር ነው።
“ቡርሳ” በትክክል እና በቅንነት እንደሚሠራ መከታተል። በዚህ የሥራ ድርሻው ባለሥልጣኑ በ“ቡርሳ”ው አማካይነት የሚረቀቁ የተሻሻሉ መመሪያዎችን ይገመግማል። እንደዚሁም ባለሥልጣኑ ብቁ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን የተሻሻሉ መመሪያዎችን ለገንዘብ ሚኒስትር እና ለፓርላማው የገንዘብ ኮሚቴ በማቅረብ እንዲተገበሩ፣ ምክር እንዲሰጥባቸው ወይም እርማት እና መመሪያዎች እንዲተላለፉ ይጠይቃል። በተጨማሪም ባለሥልጣኑ ንግዱ ላይ ቁጥጥር ያደርጋል፣ የ“ቡርሳውን ዲሬክቶሪዮን” ውይይት ያጅባል እንደዚሁም የ“ቡርሳ”ውን የሥራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ የሚያቀርበውን አቤቱታዎች ይከታተላል።
ባለሀብቶችን ለሚያማክሩና ንብረቶቻቸውን ለሚያስተዳድሩ ሥራ አስኪያጆች ፈቃድ መስጠት እንደዚሁም እነዚህ አማካሪዎችና ሥራ አስኪያጆች ግዴታቸውን ማሟላታቸውንና የሥነ ምግባር ጉድለት መድረሱን መቆጣጠር ነው። ፈቃዱን በመስጠት መዋቅር ውስጥ የባለሥልጣኑ የሥራ ድርሻዎች የሙያ ፈተናዎችን ማዘጋጀት፣ ከፈተናው ነጻ የመሆን ጥያቄዎችን ማስተናገድ፣ የሚሠለጥኑ ሠራተኞችን ዝርዝር መያዝ እና የሥልጠናውን ትምህርት መቆጣጠር ናቸው። የሥራ ፍቃድ ያላቸውን በመቆጣጠር ረገድ የሥራ ፍቃድ ያላቸው ለባለሥልጣኑ የሚሰጡትን ዘገባ ማሰባሰብ፣ በሕጉ መሠረት ግዴታቸውን መወጣታቸውን መቆጣጠር እና በሕጉ የተደነገጉት የሥነ ምግባር ጉድለቶች ተፈጽመዋል የሚል ጥርጣሬ ካለ ጉዳዩን ማስተናገድ ነው።
በባለሥልጣኑ ሥራ አስኪያጅ ትእዛዝ መሠረት የሚከተሉት ሕጐች ላይ መተላለፍ ተፈጽሞ እንደሆነ የማጣሪያ ምርመራ ያደርጋል። እነዚህም በ“ንያሮት ዔሬኽ” ሕግ መሠረት፤ በባለአደራነት (“ኔኤማኑት”) የጋራ ኢንቨስትሜንት ሕግ መሠረት፤ በ“ኢንቬስትሜንት” ምክርና የ“ኢንቬስትሜንት” ፋይሎችን በማስተዳደር ሕግ መሠረት ናቸው። እንደዚሁም ምርመራ ያደርጋል። ተጨማሪ ሕጐች መተላለፍ ተፈጽመው እንደሆነና ይህ መተላለፍ ደግሞ ከላይ ከተዘረዘሩት ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ የማጣሪያ ምርመራ ያደርጋል።
ባለሥልጣኑ ከሒሳብ አያያዝ ቢሮ ጋር በመሆን የሒሳብ “ስታንዳርድ” ተቋምን የመሠረተ ሲሆን ከቢሮው ጋር እኩል ተሳታፊ አካል በመሆን ያገለግላል። የባለሥልጣኑ ሊቀ መንበርና እና አባላቱ የሚሾሙት በገንዘብ ሚኒስትር አማካይነት ነው። ጥቂት አባላት የሚመለመሉት ከሕዝብ ሲሆኑ ከፊሉ ደግሞ የመንግሥት ሠራተኞች ናቸው። ባለሥልጣኑ የሒሳብ ባለሙያዎችን፣ የሕግ ባለሙያዎችን፣ ኢኮኖሚስቶችንና እና የአስተዳደር ሠራተኞችን በሥራ ላይ ያሠማራል።
የባለሥልጣኑ ሊቀ መንበርና እና አባላቱ የሚሾሙት በገንዘብ ሚኒስትር አማካይነት ነው። ጥቂት አባላት የሚመለመሉት ከሕዝብ ሲሆኑ ከፊሉ ደግሞ የመንግሥት ሠራተኞች ናቸው። ባለሥልጣኑ የሒሳብ ባለሙያዎችን፣ የሕግ ባለሙያዎችን፣ ኢኮኖሚስቶችንና እና የአስተዳደር ሠራተኞችን በሥራ ላይ ያሠማራል።
כיצד תשקיע נכון?לכסף שלכם מגיע יותר. ולכן, לפני שתחליטו – התייעצו, קראו, הבינו. רשות ניירות ערך מגישה לציבור המשקיעים מידע נרחב.